Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
ስለ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ
መግቢያ | ምርጫ ቦርድ አባላት |ምርጫ ቦርድ አባላት የትምህርት መረጃ ታሪክ | ምርጫ ቦርድ አደረጃጀት
 

መግቢያ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በፌደራላዊና ክልላዊ መንግስታት ገለልተኛ፣ ነጻና የማያደሉ ምርጫዎች ለማካሄድ እራሱን የቻለ አካል ሆኖ በ1985 ዓ.ም ተመሠረተ፡፡

ቦርዱ አስፈላጊ ደንብና መመሪያዎችን የማዉጣት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን መመደብ እና ማሰልጠን፣ ምርጫዉን በሚመለከት የሥነ ዜጋ ትምህርቶችን ለህብረተሰቡ መስጠት፣ የምርጫ ዉጤቶችን ማረጋገጠና ዉጤቶቹን የማሳወቅ ሀላፊነት አለበት፡፡

ቦርዱ በምርጫ ጊዜ የሚፈጠሩ መስተጓጉሎችን የማረምና የሚቀርቡለትን አቤቱታዎችን የመመርመር ስልጣን አለዉ፡፡ በምርጫ ሂደት ጊዜ የደንብና መመርያዎች መተላለፎች ከተፈጸሙ፣ ወይም የማታለል ወይም ሰላምን የማደፍረስ ደርጊቶች በምርጫ ላይ መስተጓጉሎችን እስኪፈጥሩ ድረስ ከተጋነኑ፣ የምርጫ ቦርዱ የምርጫ ዉጤቶችን የመሰረዝ እና አዲስ ምርጫዎች እንዲካሄዱ የማዘዝ ሀይል አለዉ፡፡

ቦርዱ በተጨማሪ ስታትስቲካዊ መረጃዎችን በመሰብሰብና በማጥናት እንደ አስፈላጊነቱ ለፓርላመንት የምርጫዉን ሂደት በሚመለከት ማሻሻያዎችን ያቀርባል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በብሔራዊና በክልል ደረጃ በሚካሄዱ ምርጫዎች፣ እንዲሁም የዞን፣ የወረዳ፣ እና የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫዎችን፣ የምትክ ተወካዮችን ምርጫን፣ በድጋሚ እነዲከናወኑ የተደረጉ ምርጫዎችን፣ ሪፈረንደሞችን የማስተዳደር ሀላፊነት አለዉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተግባራትና ስልጣን በ1986 ህገ መንግሰት ዉስጥ እና በአዋጅ ቁጥር 111/1987 እንዲሁም በማሻሻያዉ አዋጅ ቁጥር 438/1997 ላይ ሰፍሯል፡፡



 
   
 
   
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.