ወ/ሮ
ከበደች
እርዳቸዉ ማሙዬ
በኢትዮጵያ ብሔራዊ
ምርጫ ቦርድ ከሐምሌ
1991 ጀምሮ እያገለገሉ
ይገኛሉ፡፡ ወ/ሮ
ከበደች የኢኮኖሚና
የባህል ማስፋòያ
ድርጅት ስራ አስኪያጅ
ናቸዉ፡፡ በኢትዮጵያ
ንግድ ምክር ቤት
ዉስጥ ለ28 አመታት
ያገለገሉ ሲሆን፣
በንግድ ምክር
ቤቱ ወደ መጨረሻ
ቆይታቸዉ የኤግዚቢሽን
ከፍተኛ ባለሙያ
ሆነዉ አገልግለዋል፡፡
ወ/ሮ
ከበደች እርዳቸዉ
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ
በወጪ ንግድ ስራ
ላይ የተሰማሩ
ሴቶች ፎረም ፕሬዝደንት
እና በኢትዮጵያ
በንግድና በልዩ
ልዩ ሙያ የተሰማሩ
ሴቶች ማህበር
ምክትል ፕሬዝደንት
እንዲሁም የኢትዮጵያ
ህግ ባለሙያ ሴቶች
ማህበር ተባባሪ
አባል ናቸዉ፡፡
ወ/ሮ
ከበደች ከ1985 እስከ
1987 ድረስ በተቀመጠዉ
የህገ መንግስት
አርቃቂ ኮሚሽን
አባል ሆነዉ ሰርተዋል፡፡
ወ/ሮ ከበደች አክሽን
ፎር ዴቨሎፕመንት
ለተባለዉ መንግስታዊ
ላልሆነ ድርጅት
መሥራች እና አባል
ናቸዉ፡፡ ወ/ሮ
ከበደች የተወለዱት
በአዲስ አበባ
ነዉ፡፡
|