የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ምርጫ ቦርድ ሁሉንም
የምርጫ ሂደቶች
እንዲታዘቡ የሀገር
ዉስጥና የዉጭ
ሀገር ታዛቢዎችን
ይጋብዛል፡፡
ታዛቢዎቹ የምርጫ
ጣቢያዎችን የመጎብኘትና
የምርጫዉ ሂደትን
በሚመለከት አግባብ
ያላቸዉን መረጃዎች
የመጠየቅና የማግኘት
መብት አላቸዉ፡፡
የታዛቢዎችን
አስፈላጊነት
በመገንዘብ ቦርዱ
ለታዛቢዎቹ ዕዉቅና
የማግኘትና የሥነ
ምግባር መመሪያዎችን
አዉጥቷል፡፡
ከታዛቢ ቡድኖችን
በተጨማሪ አምስት
አድልዎ የማያደርጉ
የሕዝብ ታዛቢዎች
በእያንዳንዱ
የምርጫ ጣቢያ
በመራጮች ይመረጣሉ፡፡
ከተመረጡት የሕዝብ
ታዛቢዎች መካከል
ሁለቱ ከምርጫ
ጣቢያዉ አስተዳዳሪ
በጋራ ሆነዉ በምርጫ
ጣቢያ ደረጃ የሚቀርቡትን
አቤቱታዎች ያስተናግዳሉ፡፡
ዕጩ ተወዳዳሪዎች
በእያንዳንዱ
የምርጫ ጣቢያ
አንድ አንድ ተወካይ
የማስቀመጥ መብት
አላቸዉ፡፡