Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
የምርጫ የጊዜ ሠሌዳ
 

የፌደራልና ክልላዊ ምርጫዎች በግንቦት 7 1997 ቀን በኢትዮጵያ ይካሄዳሉ፡፡ በዚሁ እለት መራጮች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለስምንት ክልል ምክር ቤቶች እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተወካዮችን ይመርጣሉ፡፡

በብሔራዊ ደረጃ በግምት 30,000 የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋት 12፡00 እስከ ማታ 12፡00 ሰዓት ክፍት ይሆናሉ፡፡ እያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ እስከ 1,500 መራጮችን ያስተናግዳል፡፡

የሁለቱም ምርጫዎች የግዜ ሠሌዳና አስተዳደር አንድ አይነት ሲሆን ለሁለቱም አይነት የምርጫ ወረቀቶች ያተዘጋጀዉ አንድ የምርጫ ሳጥን ነዉ፡፡

በሶማሌ ክልል በ23 ብሔራዊ የምርጫ ቀበሌዎች ምርጫ የሚካሄደዉ ሐምሌ 15 1997ዓ.ም ነዉ፡፡ ይህ ልዩነት የመጣዉ በሎጂስቲካዊ ምክንያቶች ሲሆን የዚህ ክልል ሕዝቦች አርብቶ አደሮች እንደመሆናቸዉ መጠን መራጮችን ለመመዝገብ ተንቀሳቃሽ መመዝገቢያዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ይህም የቦርዱን አቅርቦቶች በስፋት መጠቀም ስለሚያስፈልገዉ በዚህ ክልል የሚደረጉ ምርጫዎች ከሌላ ክልል ምርጫዎች ጋር በአንድ አይነት የግዜ ሰሌዳ ሊደረጉ አይችልም፡፡

 
 
   
         
     
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.