የመራጮች
ምዝገባ
ይህ
ለመምረጥ ብቁ
የሆኑ መራጮች
በየነዋሪነት
ቀበሌ የምርጫ
ጣቢያዎች በመራጮች
መዝገብ ላይ የሚመዘገቡበት
የግዜ ገደብ ነዉ፡፡
ቦርዱ የመራጭ
ምዝገባ የግዜ
ገደብን ይወስናል፤
በማስረጃ የተደገፉ
ልዩ አጋጣሚዎች
ከተፈጠሩ ቦርዱ
የመራጭ ምዝገባ
የግዜ ገደቡን
ሊያስተካክል
ይችላል፡፡
በምርጫ
ህግ መሠረት ለምርጫ
ለመመዝገብ ብቁ
የሆኑ ሰዎች፡
-
•
ኢትዮጵያዊ
• በምዝገባዉ ቀን 18 ዓመት
ወይም ከዚያ በላይ
የሆናቸዉ፣
•
በምርጫዉ ቀበሌ ቢያንስ
ለስድስት ወራት
የኖሩ መሆን አለባቸዉ፡፡
(ይህ የማሟያ ነጥብ ከቀበሌያቸዉ
በፖለቲካ ስቃይ
ፍራቻ ምክንያት
ከቀበሌዉ ነዋሪነታቸዉ
ተፈናቅለዉ በቀድሞዉ
መንግስት ላይ
ትግል ሲያደርጉ
የኖሩ፣ ለሥራ
ወይም ለትምህርት
የለቀቁ ሰዎችን
አያስገድድም፡፡)
ብቁ
መራጮች ለመመዝገብ
ህጋዊ የመታወቂያ
ወረቀት ወይም
ፓስፖርት ይዘዉ
መቅረብ አለባቸዉ፡፡
መራጩ/ መራጯ መታወቂያ
ከሌለዉ ሌሎች
የቅርብ ግዜ ፎቶ
የያዙ ሰነዶችን፤
ለምሳሌ የመንጃ
ፍቃድ፣ የመኖሪያ
ፍቃድ፣ ከጦር
ሠራዊት የመልቀቂያ
ወረቀት ወይም
የተባበሩት መንግስታት
የስደተኛ ወረቀት
ከያዘ ለመመዝገብ
ብቁ ይሆናል፡፡
መራጭ እነዚህን
የመሳሰሉ ሰነዶች
ከሌለዉ ለመመዘገብ
የሚችለዉ የምርጫ
አስፌጻሚዎቹ
ማንነቱን አጣርተዉ
ካወቁ ብቻ ነዉ፡፡
አካል
ጉዳተኞችና አይነ
ስዉራን ለመመዝገብ
ሲመጡ በረዳቶች
ሊታገዙ ይችላሉ፡፡
እያንዳንዱ
የተመዘገበ መራጭ
ስሙን ወይም ስሟን፣
የትዉልድ
ቦታ፣ የተመደበለትን
ወይም የተመደበላትን
የምርጫ ጣቢያ፣
የምዝገባ ቁጥር
እና ፊርማ ወይም
የአሻራ ምልክት
የያዘ የመራጭ
ካርድ ይሰጠዋል/ይሰጣታል፡፡
መራጩ/መራጯ በምርጫ
ቀን ለመምረጠ
በሚመጣበት ጊዜ
የመራጭ ካርዱን
ይዞ መምጣት ይኖርበታል/
ይኖርባታል፡፡
የምዝገባ
ጊዜ ካለቀ በኃላ
የመራጭ መዝገቡ
ህዝብ ሊያየዉ
በሚችልበት ቦታ
በምርጫ ጣቢያዎች
ይቀመጣል፡፡
የመራጮች መዝገብ
ዓላማ እያንዳንዱ
መራጭ አንድ ግዜና
የተወሰነለት
ቦታ ብቻ እንደመረጠ
ለማረጋገጥ ብሎም
የተጭበረበረ
ምርጫን ለመከላከል
ነዉ፡፡ ማንኛዉም
ብቁ የሆነ መራጭ
በመራጮች መዝገብ
ላይ ከሌለ መምረጥ
አይችልም፡፡
የመራጭ
የመምረጥን ብቃት
በተመለከተ ማናቸዉም
አይነት ክርክሮች
ቢነሱ ፍርድ ለመስጠት
የመራጮች መዝገብ
ብቸኛ የማስረጃ
ሰነድ ሆኖ ያገለግላል፡፡