Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
የምርጫ እንቅስቃሴዎች

ዕጩ ተወዳዳሪዎች

ማንኛዉም የተመዘገበ መራጭ የሚከተሉትን ነጥቦች ካሟላ ዕጩ ተወዳዳሪ ሊሆን ይችላል፡፡

   ኢትዮጵያዊ፣
  ሊወዳደሩበት ያሰቡበትን ክልል ቋንቋ መናገር መቻል፣
በምርጫዉ ቀን ቢያንስ 21 የሆነዉ/የሆናት፣

ሊወዳደሩበት ባሰቡበት የምርጫ ክልል ከምርጫ ቀን ቀደም ብሎ በነዋሪነት ለሁለት ዓመት የቆዩ ወይም ለመወዳደር ባሰቡበት ወረዳ ወይም ከተማ የተወለዱ መሆን አለባቸዉ፡፡

የግል ተወዳዳሪዎች በምርጫ ቀበሌዉ ለመምረጥ ብቁ ከሆኑ ነዋሪዎች 1000 የድጋፍ ፊርማዎችን መሰብሰብ አለባቸዉ፡፡ በፖለቲካ ድርጅቶች የሚቀርቡ ተወዳዳሪዎች ለመመዝገብ የድጋፍ ፊርማዎችን መሰብሰብ አይጠበቅባቸዉም፡፡ የተመዘገቡ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ምልክታቸዉን እራሳቸዉ መምረጥ ይችላሉ፡፡ የፓርቲ ምልክቶች ባለቤትነት በቦርዱ የተረጋገጠ ነዉ፡፡

ከ35 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተዉጣጡ ተወዳዳሪዎች እንዲሁም 353 የግል ተወዳዳሪዎች በጠቅላላዉ 1845 ተወዳዳሪዎች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎች ለመወዳደር ተመዝግበዋል፡፡

ከ33 የፖለቲካ ፓርቲዎች የተዉጣጡ ተወዳዳሪዎች እንዲሁም 70 የግል ተወዳዳሪዎች በጠቅላላዉ 3662 ተወዳዳሪዎች ለክልል ምክር ቤት መቀመጫዎች ይወዳደራሉ፡፡

 

 
   
     
       
         
       
1 |2|3|4
         
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.