Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
የምርጫ እንቅስቃሴዎች

የይግባኝ ጥያቄዎችና አቤቱታዎች

የመራጭ ምዝገባን፣ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን ምዝገባን፣ በምርጫ ሳጥኖችን መምረጥና የምርጫ ወረቀቶችን ቆጠራ በሚመለከቱ አቤቱታዎች ላይ በየደረጃዉ ዝርዝር ሥርዓቶች ወጥተዋል፡፡

የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴዎች

ምርጫዉ ሁለት ቀን እስኪቀረዉ ድረስ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ይቻላል፡፡ ማንኛዉም ተወዳዳሪ ደጋፊዎቹን ስብሰባ የመጥራትና ሰላማዊ ሰልፎችን የማድረግ መበት አለዉ፡፡ የከተማዉን አስተዳደር ወይም ማዘጋጃ ቤትን ከማሳወቅ በስተቀር አስቀድሞ ፈቃድ መጠየቅ አያስፈልግም፡፡

ምርጫ

እያንዳንዱ መራጭ በተመዘገበበት የምርጫ ጣቢያ በተዘጋጁት ድምጽ መሥጫ ሳጥኖች ዉስጥ ድምጹን ይሰጣል፡፡ መራጮች ለመምረጥ የመራጭ ካርድ እና የመታወቂያ ወይም ሌላ ለመታወቂያነት ሊያገለግሉ የሚችሉ ሰነዶቻቸዉን ይዘዉ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ ማንነታቸዉም ከተረጋገጠ በኃላ መራጮች ፊርማቸዉን ወይም የአሻራ ምልክታቸዉን በምርጫ መዝገብ ላይ ማስፈር አለባቸዉ፡፡

መራጮች በድምፅ መስጫ ክፍል ዉስጥ በድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ለሚመርጡት ተወዳዳሪ X ምልክት በማድረግ ድመጻቸዉን ይሰጣሉ፤ ማንበብና መጻፍ የማይችሉ መራጮች የአሻራቸዉን ምልክት ይጠቀማሉ፡፡ መራጮች የምርጫ ጣብያዉን ከመልቀቃቸዉ በፊት ጣታቸዉ ላይ ቀለም ማስቀባት ይኖርባቸዋል፤ ይህ እርምጃ አንድ ሰዉ ከአንድ በላይ ድምጽ እንዳይሰጥ ይከላከላል፡፡

አካል ጉዳተኞች መራጮች የሚፈልጉትን ረዳት ይዘዉ የመምጣት መብት አላቸዉ፡፡

ምርጫዉ ካለቀ ከጥቂት ቆይታ በኃላ የምርጫ ወረቀቶች ቆጠራ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተሰጠ መመሪያ መሠረት ይጀመራል፡፡

የምርጫ ጣቢያ መመሪያ መፅሐፍ
 
 
     
     
 
 
1 |2|3|4
   
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.