Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
የምርጫ ሥርዓቱ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት የታወጀዉ ህዳር 30 1986ዓ.ም ስራ ላይ በዋለዉ ህገመንግስት ስር ነዉ፡፡ ይህ የዘጠኝ ነጻና በከፊል ራሳቸዉን ችለዉ የሚተዳደሩ፣ የሕዝብ አሰፋፈራቸዉ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ ላይ መሰረት በማድረግ የተዋቀሩና አዲስ አበባን መዐከል ያደርጉ ብሔራዊ ክልሎች ፌደሬሽን ነዉ፡፡ የፌደሬሽኑ መንግስት አባላት፡ ትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማልያ፣ ቤንሻንጉል/ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ ሐረር እና የደቡብ ክልል ብሔር፣ ብሔረቦችና ሕዝቦች ክልል ናቸዉ፡፡ የሀገሪቱ ህዝብ ብዛት 72.4 ሚልዮን ሲሆን የቆዳ ስፋቷ 1.13 ስክዌር ኪሎሜትር (437,794 ስክዌር ማይል) ነዉ፡፡  

ህገመንግስቱ የመድበለ ፓርላመንታዊ ሥርዓትን ያቋቋመ ሲሆን፣ በስሩም ሁለት ምክር ቤቶች ማለትም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌደሬሽን ምክር ቤትን ይይዛል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፌደራሉ መንግስት ከፍተኛዉን ስልጣን ሲይዝ ሁሉንም የፌደራል ጉዳዮች አስመልክቶ ህግ የማዉጣት ሀይል ያለዉ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፤ ሁሉን አቀፍ፣ ነፃ፣ ቀጥተኛ፣ ትክክለኛ በሆነ፣ ድምፅ በሚስጥር በሚሰጥበት ሥርዓት በየአምስት ዓመቱ በሕዝቡ ይመረጣሉ፡፡ የምክር ቤቱ አባላት በአንድ የምርጫ ክልል ዉስጥ ከሌሎች ተወዳዳሪዎች መካከል አብላጫ ድምፅ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ይመረጣሉ፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ቁጥር የሕዝብ ብዛትንና በልዩ ትኩረት ዉክልና የሚሰጣቸዉ አናሳ ብሔረሰቦችና ሕዝኖችን ቁጥር መሰረት በማድረግ በአሁኑ ጊዜ 547 ሲሆኖ ከዚህ ዉስጥ አናሳ ብሔረሰቦች 22 መቀመጫ ይኖራቸዋል፡፡

ጠቃላይ ሚሊስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ይመረጣሉ፡፡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘዉ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ያገኙት ጣምራ የፖለቲካ ድርጅቶች የመንግስትን ሥልጣን ይረከባል/ይረከባሉ፡፡

   
     
   
 
1 | 2
   
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.