Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
የምርጫ ሥርዓቱ
 

የፌደሬሽን ምክር ቤት

በህገመንግስቱ ስር 110 መቀመጫ ያለዉ የፌደሬሽኑ ምክር ቤት በፌደራሉ መንግስት አባል ክልሎች የሚገኙት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች የሚልኩዋቸዉ አባላት የሚወከሉበት ምክር ቤት ነዉ፡፡ እያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ ቢያንስ አንድ ተወካይ ይኖረዋል፤ በተጨማሪም የብሔር ወይም ብሔረሰቡ አንድ ሚሊዮን ህዝብ አንድ ተጨማሪ ወኪል ይኖረዋል፡፡

የፌደሬሽን ምክር ቤት አባላት በክልል ምክር ቤቶች ይመረጣሉ፤ የክልል ምክር ቤቶች በራሳቸዉ ወይም በሕዝብ በቀጥታ እንዲመረጡ በማድረግ የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል እንዲወከል ያደርጋሉ፡፡ ይህ አሠራር በተግባር ላይ ዉሎ አያዉቅም፡፡ በክልል ደረጃም የፌደሬሽን ምክር ቤት ተወካዮችን ቀጥተኛ ምርጫዎችን የማድረግ ህግ አልቀረበም፡፡

ሁለቱ በፌደራል መንግስት ምክር ቤቶች የፌደሬሽኑን ፕሬዚደንት ማለትም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ርዕሰ ብሔርን በጋራ ይመርጣሉ፡፡ ፕሬዚደንቱ በዋናነት የሚኖራቸዉ የክብር ስልጣን ሲሆን የሥራ ዘመናቸዉ ስድስት አመት ይሆናል፡፡

በአስተዳደር ደረጃ የኢትዮጵያ ዘጠኝ መንግስታት በ70 ዞኖች ይከፈላሉ፡፡ ዞኖቹም ከ600 ወረዳዎች የተዋቀሩ ሲሆኑ በግምት በ28,000 መንደሮች ይከፈላል፡፡ ህገመንግስቱ እስከ 550 የቀበሌ ምራጫዎች ሊኖሩ እንደሚችል ቢያስቀምጥም በግዜዉ ያሉት ግን 547 ናቸዉ፡፡

የክልል ምክር ቤቶች

የዘጠኙ ክልሎችና የአዲስ አበባ አስተዳደር የክልል ምክር ቤቶች ምርጫዎችም የሚካሄዱት አብላጫ ድምፅ ያገኘ ተወዳዳሪ አሸናፊ በሚሆንበት የምርጫ ሥርዓት ነዉ፡፡ ነገር ግን ከአንድ የምርጫ ክልል ከእንድ በላይ ተወዳዳሪዎች ሊመረጡ ይችላሉ፡፡ የእያንዳንዱ የምርጫ ክልል የመቀመጫ ብዛት የሚወሰነዉ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሲሆን የክልላዊ ህገመንግስቶች ወይም ህጎችን መሰረት በማድረግ ነዉ፡፡ በአሁኑ ግዜ ያለዉ በየክልሎች የሚገኘዉ የመቀመጫ ብዛት እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡ በአዲስ አበባ 6፣ በትግራይ 4፣ በአማራ 2፣ በኦሮሚያ 3፣ በሶማሊያ 3፣ በቤንሻንጉል/ጉሙዝ 10፣ በደቡብ ክልል ብሔር ብሔረቦች መንግስት 3 መቀመጫዎች፣ በጋምቤላና በሐረር የምርጫ ቀበሌዎች በየግዜዉ በቁጥር የሚለያዩ መቀመጫዎች አላቸዉ፡፡

 
     
   
1 | 2
 
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.