የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ምርጫ
ቦርድ አባላት
ቦርዱ
የተዋቀረዉ ጠቅላይ
ሚኒሰትሩ በሚያቀርቧቸዉ፣
በህዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት በሚሾሙ
ሰባት አባላት
ሲሆን አባላቱም
ለህዝብ ተወካዮች
ምክር ቤት ነዉ፡፡
የቦርድ
አባላት የሚመረጡት
ለህገ መንግስቱ
ያላቸዉን አክብሮት፣
ከፖለቲካ ፓርቲዎች
ጋር ግንኙነት
የሌላዉ መሆኑንና
የስራ ብቃታቸዉን
መሠረት በማድረግ
ነዉ፡፡
የቦርዱ
ሊቀመንበር የሚመረጠዉ
በተወካዮች ምክር
ቤት ሲሆን ለቦርዱ
ጠቅላላ አስተዳደርና
እንቅስቃሴ ሀላፊነት
ይኖራቸዋል፡፡
የቦርዱ
ምክትል ሊቀመንበር
የሚመረጠዉ ከአባላቶቹ
መካከል ሲሆን
ሊቀመንበሩ በማይኖሩበት
ግዜ ሥራቸዉን
ይሰራል፡፡
ቦርዱ
ስራ አስፈጻሚና
በምክትል ስራ
አስፈጻሚ የሚመራ
ጽህፈት ቤት ይኖረዋል፡፡
ሁለቱም የሚመረጡት
በስራ ልምዳቸዉና
በችሎታቸዉ ነዉ፡፡
በጠቅላይ ሚኒሰትሩ
ጥቆማ በተወካዮች
ምክር ቤት ሊመረጡም
ይችላሉ፡፡ ስራ
አስፈጻሚዉ የመምረጥ
መበት የሌለዉ
የቦርዱ አባልና
የቦርዱ ሴክረተሪያትም
ሆኖ ያገለግላል፡፡
የቦርዱ
አባላት በስራ
አፈጻጸማቸዉ
ገለልተኛና እራሳቸዉን
የቻሉ የሙያ ሰዎች
ናቸዉ፡፡
የቦርድ
ዉሳኔዎች የሚወሰኑት
በአብላጫ ድምጽ
ነዉ፡፡ አቻ ዉጤት
በሚኖርበት ግዜ
የቦርዱ ሊቀመንበር
ወሳኙን ምርጫ
ያደርጋል፡፡
ቦርዱ በየሳምንቱ
ስብሰባ የሚያደርግ
ሲሆን ስብሰባዉን
ለማስኬድ የሚያስፈልገዉ
ኮረም የአራት
አባላት መሟላት
ይሆናል፡፡