መጋቢት 4 ቀን
1997 ዓ.ም.
የአውሮፓ
ሕብረት
ምርጫውን ለመታዘብ
የሚያስችለውን
ስምምነት
ከኢትዮጵያ መንግስት
ጋር ተፈራረመ
የአውሮፓ
ሕብረት በመጪው
ግንቦት ወር በሚካሄደው
የሕዝብ ተወካዮችና
የክልል ምክር ቤቶች
አባላት ምርጫ ታዛቢዎችን
ለማሰማራት የሚያስችለውን
የመግባቢያ ስምምነት
ከኢትዮጵያ መንግስት
ጋር ተፈራረመ፡፡
የውጭ ጉዳይ
ሚኒስቴር ዴኤታ
ዶ/ር ተቀዳ አለሙ፣
የኢትዮጵያ ብሔራዊ
የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር
አቶ ከማል በድሪና
በኢትዮጵያ የአውሮፓ
ሕብረት ልዑክ ተጠሪ
አምባሳደር ቲም
ክላሪክ ስምምነቱን
ፈርመዋል፡፡
በአይነቱ
የመጀመሪያ የሆነው
ይኸው ስምምነት
የአውሮፓ ሕብረት
ታዛቢዎቹን በተለያዩ
የአገሪቱ ክፍሎች
በማሰማራት በነፃ
ለመታዘብ ያስችለዋል፡፡
የሕብረቱ
ተወካዮች የድምፅ
አሰጣጥ ሂደቱን
የሚታዘቡ ሲሆን
የምርጫ አስፈፃሚዎችን
ያነጋግራሉ፣ ተዛማጅ
ሰነዶችና መረጃዎችን
ይመለከታሉ፡፡
አቶ ከማል
በድሪ በዚሁ ጊዜ
እንዳሉት የሕብረቱ
ተወካዮች ኃላፊነታቸውን
በሚገባ ይወጡ ዘንድ
ቦርዱ አስፈላጊውን
ትብብርና ድጋፍ
ለማድረግ ዝግጁ
ነው፡፡