የፕሬስ
መግለጫ (መጋቢት
4 ቀን 1997 ዓ.ም.)
የፓርቲዎች የጋራ
መድረክ ቅሬታዎችን
በአፋጣኝ ለመፍታት
አስችሏል፡፡
በቅርቡ
የተቋቋመው የፖለቲካ
ፓርቲዎች የጋራ
መድረክ ከመጪው
ምርጫ ጋር በተያያዘ
የሚቀርቡ ቅሬታዎችን
በአፋጣኝ ለመፍታት
እንዳስቻለ የኢትዮጵያ
ብሔራዊ የምርጫ
ቦርድ ሰብሳቢ ገለፁ፡፡
ሰብሳቢው
አቶ ከማል በድሪ
በትናንትናው ዕለት
በቦርዱ ጽሕፈት
ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ
መግለጫ እንዳስታወቁት
ቦርዱ ከጋራ መድረኩ
አባላት ጋር በመሆን
በተለያዩ ቦታዎች
በዕጩ ተወዳዳሪዎችና
ደጋፊዎቻቸው ላይ
ደረሱ የተባሉትን
የመብት መጣስ በማጣራት
ውሣኔዎችን እየሰጠ
ይገኛል፡፡
ቦርዱ
ከገዥው ፓርቲና
ተቃዋሚዎች የሚደርሰውን
አቤቱታ በእኩል
መልክ እያስተናገደ
ስለመሆኑ ተጠይቀው
ሲመልሱ ቦርዱ እስካሁን
ድረስ ቀርበውለት
ውሣኔ ከሰጠባቸው
ጉዳዮች ውስጥ አብዛኞቹ
በተቃዋሚ ፓርቲ
አባላት የቀረቡ
ናቸው ብለዋል፡፡
በቅርቡ
በብሔራዊ የምርጫ
ቦርድ የወጣውን
የአገር ውስጥ ታዛቢዎች
የዕውቅና ፈቃድ
አሰጣጥ መመሪያን
አስመልክተው እንደተናገሩት
ማንኛውም ምርጫውን
ለመታዘብ የሚፈልግ
የአገር ውስጥ ታዛቢ
ገለልተኛ የሆነና
ድርጅቱ ሲመሰረት
ምርጫን ለመታዘብ
የሚያስችል ከመንግሥት
የተሰጠ ፈቃድ ማቅረብ
ይኖርበታል፡፡
ይህ አሠራር
ለምርጫው በታዛቢነት
የሚሰማሩ አካላት
ገለልተኛ የሆኑና
ከጉዳዩ ጋር ቅርበት
ያለው ሥራ በመሥራት
ላይ የሚገኙ እንዲሆኑ
ለማድረግ እንጂ
ማናቸውምንም ወገን
ከታዛቢነት ለማራቅ
ታስቦ የተዘጋጀ
አለመሆኑን አስረድተዋል፡፡
አንዳንድ
መንግሥታዊ ያልሆኑ
ድርጅቶች ከፖለቲካ
ፓርቲዎች ጋር ግንኙነት
እንዳላቸው የጠቆሙት
አቶ ከማል ምርጫ
ቦርድ ታዛቢ አካላት
ከማንኛውም የፖለቲካ
ወገንተኝነት የፀዱ
መሆናቸውን የማረጋገጥ
ኃላፊነት አለበት
ብለዋል፡፡
ለፖለቲካ
ፓርቲዎችና ለግል
ተወዳዳሪ ዕጩዎች
የተመደበውን የገንዘብ
ድጋፍ አስመልክቶ
ለተነሳው ጥያቄ
በሰጡት መልስም
ማንኛውም የፖለቲካ
ፓርቲ ሆነ የግል
ተወዳዳሪ ዕጩ 400
የአሜሪካን ዶላር
የተመደበለት ሲሆን
ይህም ድጋፍ በዓይነት
የሚደረግ እንጂ
በጥሬ ገንዘብ የማይሰጥ
መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የግል
ተወዳዳሪዎች የተመደበላቸው
ገንዘብ በቦርዱ
በተመረጡት ሶስት
ማተሚያ ቤቶች ፖስተሮችና
በራሪ ወረቀቶችን
እንዲታተሙላቸው
መጠየቅ እንደሚችሉ
አስረድተዋል፡፡
ከለጋሽ ሀገራት ጋራ
በተደረሰው ስምምነት
መሠረት ለማንኛውም
ዕጩ ተወዳዳሪ የጥሬ
ገንዘብ ድጋፍ እንደማይደረግ
አቶ ከማል ጨምረው
ገልፀዋል፡፡
የከፍተኛ
ትምሕርት ተቋማት
ተማሪዎች የምርጫ
ሂደት፣ ጥፋት በፈፀሙ
የምርጫ አስፈፃሚዎች
ላይ ስለተወሰደ
እርምጃና በኢትዮጵያ
ሰብዓዊ መብቶች
ጉባዔ በወጣው ሪፖርት
ዙሪያ ጥያቄዎች
ቀርበው በቦርዱ
ባለሥልጣናት ምላሽ
ተሰጥቶበታል፡፡