Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
   
 

የፕሬስ መግለጫ (ሚያዝያ 5 ቀን 1997 ዓ.ም.)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ኦብኮ ባቀረበው ቅሬታ ላይ ውሳኔ ሰጠ

      የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በትናንትናው ዕለት (ሚያዝያ 4) ባካሄደው ስብሰባ የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ (ኦብኮ) ባቀረበው ቅሬታ ላይ ውሣኔ ሰጠ፡፡

      ኦብኮ ሚያዝያ 1 ቀን 1997 ዓ.ም. በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ የምርጫ ክልል አባሎቼና ደጋፊዎቼ የምርጫ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እንዳሉ የመብት መጣስ ድርጊት ተፈፅሞባቸዋል ሲል ለቦርዱ ባቀረበው ቅሬታ መሠረት ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን እስፍራው ድረስ አጣሪ ቡድን በመላክ አጣርቷል፡፡

      በዕለቱ ለተፈጠረው ግጭት መንስዔ የሆነው የኦብኮ ደጋፊዎች ከምርጫ ቅስቀሳ በፊት  ጉዳዩን ለሚመለከታቸው አካላት ባለማሳወቃቸውና ቅስቀሳውም በትምሕርት ቤት አካባቢ ተማሪዎች በሚወጡበት ሰዓት በመከናወኑ መሆኑን የአጣሪ ቡድኑ ሪፖርት ያስረዳል፡፡

      በረብሻው ምክንያትም ከፖሊስ፣ ከኦብኮ አባላትና እንዲሁም ከሰላማዊ ሕዝብ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱን ቡድኑ አረጋግጧል፡፡

      ቦርዱ የቀረበለትን ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ ማንኛውም ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ የሚደረግ የምርጫ ቅስቀሳ በሕጉ መሠረት በቅድሚያ ለሚመለከታቸው አካላት ማሳወቅ እንዳለበትና በጀልዱ አካባቢ የሚደረገው ቅስቀሳም ሁከትና ረብሻን የሚያነሳሳ መሆን እንደሌለበት አሳስቧል፡፡

      ቦርዱ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደፊት መግለጫ እስኪሰጥበት ጊዜ ድረስ በጀልዱ ከተማ በገበያ መሃል የምረጡኝ ቅስቀሳ በማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ እንዳይካሄድ ወስኗል፡፡

      ከዚህ በተጨማሪም ማንኛውም በባንድም ሆነ በድምፅ ማጉያ የሚካሄድ በኪነት የታጀበ ቅስቀሳ በምርጫው ላይ ብቻ ያተኮረ እንዲሆንና ሕዝብን ለአመጽ የሚያነሳሳ እንዲሁም ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጭ መሆን እንደሌለበት ቦርዱ ወስኗል፡፡

      ይህንኑም ውሣኔ በጀልዱ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ቦርዱ ወስኗል፡፡

 

 
     
     
       
   
       
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.