የፕሬስ መግለጫ
(ሚያዝያ 10 ቀን 1997 ዓ.ም.)
በየምርጫ ጣቢያው
ሁለት ተጨማሪ የምርጫ
አስፈፃሚዎች ይመደባሉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ
የምርጫ ቦርድ በመጪው
ግንቦት 7 የሚካሄደውን
አገራዊና ክልላዊ
ምርጫ በተሳካ መልኩ
ለማከናወን እንዲያስችል
በየምርጫ ጣቢያው
ሁለት ተጨማሪ የምርጫ
አስፈፃሚዎችን
ለመመደብ ወሰነ፡፡
ይህም በየምርጫ ጣቢያው
የሚኖሩትን የምርጫ
አስፈፃሚዎች ቁጥር
ወደ አምስት ከፍ
ያደርገዋል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ
ከማል በድሪ እንደተናገሩት
የምርጫ አስፈፃሚዎች
ቁጥር መጨመር በምርጫ
ቀን በአስፈፃሚዎች
ላይ የሚኖረውን
የሥራ ጫና ከመቀነሱም
በላይ ለመራጮች
የተቀላጠፈ አገልግሎት
ለመስጠት ያስችላል፡፡
ሁለቱ ተጨማሪ የምርጫ
አስፈፃሚዎች የመራጮች
ማረጋገጫ ቀለም
የመቀባትና የድምፅ
መስጫ ወረቀትን
የማደል ሥራ ሲያከናውኑ
ነባሮቹ ሦስት አስፈፃሚዎች
ደግሞ የመራጮችን
መዝገብ የማመሳከርና
ማብራሪያ የመስጠት
ሥራን ይሰራሉ፡፡
የምርጫ አስፈፃሚዎችን
ቁጥር የመጨመሩ
ሃሣብ በፖለቲካ
ፓርቲዎች የጋራ
መድረክ ቀርቦ ሙሉ
ተቀባይነት ማግኘቱንም
አቶ ከማል ጨምረው
ገልፀዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በርካታ
ድምፅ ሰጪዎች የተመዘገቡባቸውን
የምርጫ ጣቢያዎች
በመክፈል 736 አዲስ
የምርጫ ጣቢያዎች
እንደሚቋቋሙ የቦርዱ
ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
የቦርዱ ጽሕፈት ቤት
ምክትል ኃላፊ አቶ
ተስፋዬ መንገሻ
እንደገለፁት የአዳዲስ
ጣቢያዎች መቋቋም
በተወሰኑ ጣቢያዎች
ላይ የሚኖረውን
መጨናነቅ ስለሚቀንስ
ምርጫው በተሳካ
ሁኔታ እንዲካሄድ
ያግዛል፡፡ የየምርጫ ክልል አስተባባሪዎች
ለተጨማሪ ጣቢያዎች
የሚያስፈልገውን
የሰው ኃይል መልምለው
እንዲያሰለጥኑ
ትዕዛዝ መተላለፉንም
አስረድተዋል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የሶማሌ
ክልልን ሳይጨምር
በመላ ሃገሪቱ 28,811
የምርጫ ጣቢያዎች
ይገኛሉ፡፡