የፕሬስ መግለጫ
(ሚያዝያ 18 ቀን 1997 ዓ
ም)
ቦርዱ 20,000 የምርጫ
ማረጋገጫ ቀለም
ተረከበ
የኢትዮጵያ
ብሔራዊ የምርጫ
ቦርድ በመጪው ምርጫ
የመራጮችን የአውራ
ጣት ለመቀባት የሚያገለግል
20000 የድምፅ ሰጪዎች
ማረጋገጫ ቀለም
ተረከበ፡፡ ለምርጫው
በአጠቃላይ የሚያስፈልገው
240,000
ቀለም
ሲሆን ቀሪው በሳምንት
ጊዜ ተጠናቆ እንደሚገባ
ይጠበቃል፡፡
በሕንድ
ኩባንያ አማካኝነት
ተገዝቶ እየገባ
ያለው አዲሱ ቀለም
ከዚህ በፊት ተገዝቶ
ቶሎ የሚለቅ በመሆኑ
ጥቅም ላይ እንዳይውል
በተወሰለው ቀለም
የተተካ ነው፡፡
የቦርድ
ሰብሳቢ አቶ ከማል
በድሪ እንደገለፁት
ከዚህ በፊት ተገዝቶ
የነበረው ቀለም
12 በመቶ የሲልቨር
ናይትሬት ይዘት
ሲኖረው የአሁኑ
ግን 25 በመቶ ሲልቨር
ናይትሬት የያዘ
ነው ብለዋል፡፡
ይህም ቀለሙ ቶሎ
እንዳይለቅ ያደርገዋል
ተብሏል፡፡
ለቀለሙ
ግዥ የሚያስፈልገው
ወጪ ለመጪው ምርጫ
ለጋሾች በሰጡት
ገንዘብ የተሸፈነ
ሲሆን አዲሱን ቀለም
ያስመጣው ኩባንያ
ቀለሙን ለቀየረበት
ተጨማሪ ወጪ አልጠየቀም፡፡
አዲሱ
ቀለም በፖርቲዎች
የጋራ መድረክ ተቀባይነትን
አግኝቷል፡፡ የጋራ
መድረኩ ከዚህ በፊት
የተገዛውን ቀለም
ቶሎ የሚለቅ በመሆኑ
ሥራ ላይ እንዳይውል
መጠየቁ ይታወሳል፡፡