የፕሬስ
መግለጫ (ሚያዝያ
19 ቀን 1997 ዓ ም)
ለምርጫ
አስፈፀሚዎች ሥልጠና
ተሰጠ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ
የምርጫ ቦርድ በመጪው
ምርጫ ተግባራዊ
የሚደረጉ አዳዲስ
አሰራሮችን በተመለከተ
ለምርጫ ክልል ምርጫ
አስፈፃሚዎች የሁለት
ቀናት ሥልጠና ስጠ፡፡
ቁጥራቸው 180 የሚሆኑ
የምርጫ ክልል አስፈፃሚዎች
በመጀመሪያው ዙር
ሥልጠና የተሳተፉ
ሲሆን ቀሪዎቹም
በቀጣዮቹ ሦስት
ዙሮች ሥልጠናውን
ይወስዳሉ፡፡
የቦርዱ ጽሕፈት ቤት
ምክትል ኃላፊ አቶ
ተስፋዬ መንገሻ
እንደገለፁት የሥልጠናው
ዋና ዓላማ ከዚህ
በፊት በተሰጡ ሥልጠናዎች
ያልተሸፈኑ ከድምፅ
አሰጣጥ፣ ቆጠራና
ውጤት አገላለፅ
ጋር በተያያዙ ጉዳዩች
ላይ አስፈፃሚዎች
ግንዛቤ እንዲኖራቸው
ለማድረግ ነው፡፡
በሥልጠናው በየምርጫ
ጣቢያው ስለሚመደቡ
ሁለት ተጨማሪ የምርጫ
አስፈፃሚዎች አመላመል፣
ሥልጣናና ምደባ
ገለፃ የተደረገ
ሲሆን የምርጫውን
ምስጢራዊነት ለመጠበቅ
ያስችላል ተብሎ
የታመነበት በድምፅ
መስጫ ወረቀት ጀርባ
ስለሚደረገው ባለ
ቁጥር ማሕተም አጠቃቀም
ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የምርጫ ክልል የምርጫ
አስፈፃሚዎች በሥራቸው
ያሉትን የምርጫ
ጣቢያ አስፈፃሚዎች
ተመልሰው ያሰለጥናሉ፡፡
በአገሪቱ የሶማሌ
ክልልን ጨምሮ ከ100,000-120,000 ሕዝብ ያላቸው
547 የምርጫ ክልሎች
ይገኛሉ፡፡