ሚያዝያ
25 ቀን 1997 ዓ.ም.
319አለም አቀፍ ታዛቢዎች
ምርጫውን ይታዘባሉ
በኢትዮጵያ ግንቦት
7 ቀን 1997 ዓ.ም. የሚካሄደውን
የፌዴራልና የክልል
ምክር ቤቶች ምርጫ
ለመታዘብ 319የውጭ
ታዛቢዎች እንደሚሰማሩ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ
የምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ
ከማል በድሪ ባለፈው
ሰኞ (ሚያዝያ 24) ለጋዜጠኞች
እንደገለፁት አብዛኞቹ
ታዛቢዎች ከአውሮፓ
ሕብረት፣ የካርተር
ማዕከል፣ አፍሪካ
ሕብረትና ዓረብ
ሊግ የተውጣጡ ሲሆኑ
ቀሪዎች ከተለያዩ
ሀገራትና ኤምባሲዎች
የተወከሉ ናቸው፡፡
ታዛቢዎቻቸውን ከሚያሰማሩ
አገራት መካከል
ዩናይትድ ስቴትስ፣
ሕንድ፣ ቻይና፣
ጃፓንና ቱርክ ይገኙበታል፡፡
እነዚህ አገራት ታዛቢዎቻቸውን
የሚያሰማሩት በኢትዮጵያ
መንግሥት በተደረገላቸው
ጥሪ መሆኑንም አቶ
ከማል ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የሀገር ውስጥ ታዛቢዎችን
ለምን ከለከላችሁ
ተብለው የተጠየቁት
ሰብሳቢው ቦርዱ
የሀገር ውስጥ ታዛቢዎችን
እንዳልከለከለ
ነገር ግን ምርጫውን
ለመታዘብ ለሚፈልጉ
የሀገር ውስጥ ድርጅቶች
በምርጫ ሕጉ መሠረት
መመሪያ ማውጣቱን
ጠቁመዋል፡፡
በመመሪያው መሠረት
አንድ የሀገር ውስጥ
ታዛቢ ድርጅት ገለልተኛ
መሆንና ድርጅቱ
ሲመሰረት ምርጫን
መታዘብ እንደ አንድ
አላማው ያስቀመጠ
መሆን ይኖርበታል፡፡
የጋዜጠኞችን የፈቃድ
አሰጣጥ በተመለከተ
በሕጉ መሠረት ጋዜጠኛ
መሆናቸው በማስታወቂያ
ሚኒስቴር ሲረጋገጥ
ቦርዱ በምርጫ ጣቢያዎች
መዘገብ የሚያስችላቸውን
ፈቃድ ይሰጣቸዋል
ብለዋል፡፡
በፖለቲካ ፓርቲዎች
የሚቀርቡ ቅሬታዎችን
አፈታት በተመለከተ
ለቀረበላቸው ጥያቄ
መልስ ሲሰጡ ቦርዱ
እስከአሁን ሲቀርቡለት
ለነበሩና እየቀረቡለት
ላሉ አቤቱታዎች
በየደረጃው በተቋቋሙ
የፖለቲካ ፓርቲዎች
መድረኮችና ከዋናው
መሥሪያ ቤት አጣሪ
ቡድን በመላክ ችግሩን
ከመረመረ በኋላ
መፍትሔ እየሰጠ
ይገኛል ብለዋል፡፡
ከተቃዋሚ የፖለቲካ
ፓርቲዎች በቀረቡ
ጥቆማዎች አማካኝነት
ከምርጫ ሕጉ ውጭ
ሲሰሩ የተገኙ የምርጫ
አስፈፃሚዎች ከሥራ
እንዲሰናበቱና
በሕግ እንዲጠየቁ
እየተደረገ መሆኑንም
አቶ ከማል አብራርተዋል፡፡