ግንቦት
7 ቀን 1997 ዓ.ም. ለሚደረገው
ምርጫ ጠቃሚ መረጃዎች
የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጽ/ቤት ለመጪው ምርጫ
ቀን እንዲውል የተለያዩ
ቁሳቁሶችን በሀገሩ
ውስጥ ለሚገኙ 31(ዐዐዐ
የምርጫ ጣቢያዎች
ልኳል፡፡
•
28.6 ሚሊዮን የድምፅ
መስጫ ወረቀት (25.6
ሚሊዮን ህዝብ በመራጭነት
ተመዝግቧል)
•
124,000 የምርጫ ማረጋገጫ
ቀለም
•
2,815 እስክሪብቶዎች
•
11,260 ስለምርጫው ሂደት
ገለፃ የሚያደርጉ
ፓስተሮች
155,000 የምርጫ
አስፈፃሚዎች በ31,000
የምርጫ ጣቢያዎች
በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡
1689 በምርጫ ክልሎች
ውስጥ የሚሰሩ የምርጫ
አስፈፃሚዎች አሉ፡፡
319
የውጭ ታዛቢዎች
ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
ከእነዚህም ታዛቢዎች
መካከል 150 የሚያህሉት
ከአውሮፓውያን
ህብረት እና 50 ታዛቢዎች
ከካርተር ማዕከል
የመጡ ናቸው፡፡
ከአፍሪካ
ህብረት፣ ከአረብ
ሊግ፣ ከቻይና፣
ከተርኪ፣ ከሩሲያ
እና ከኢንዲያ ምርጫውን
ለመታዘብ ታዛቢዎች
ተጋብዘዋል፡፡
የድምፅ
መስጫ ወረቀቶችና
የተለያዩ ቁሳቁሶች
ወደ ምርጫ ጣቢያዎች
በመኪና ከመጓጓዝዛቸው
በተጨማሪ የምርጫ
ቦርድ በጋምቤላ
ክልል ጀልባዎችን
ለማጓጓዣነት ተጠቅሟል፡፡
በኢትዮጵያ
የሚገኙ የሀይማኖት
ተቋማት ምርጫውን
ለመታዘብ ፈቃድ
እያገኙ ነው፡፡
እስካሁን ከኦርቶዶክስ
ቤ/ክርስቲያን 186
የሚያህሉ ሰዎች
የምርጫው ታዛቢ
ለመሆን ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
267 ታዛቢዎች ከወንጌላዊያን
ቤ/ክርስቲያን እና
13 ታዛቢዎች ከኢትዮጵያ
እስልምና ጉዳዮች
ምክር ቤት ፈቃድ
አግኘተዋል፡፡
የድምፅ
መስጫ ወረቀቶችና
የተለያዩ ቁሳቁሶች
ወደ ምርጫ ጣቢያዎች
በመኪና ከመጓጓዛቸውም
በተጨማሪ ምርጫ
ቦርድ በጋምቤላ
ክልል ጀልባዎችን
ለማጓጓዣነት ተጠቅሟል፡፡
በተጨማሪም
በአማራ ክልል እና
በሰሜን ተራራ አካባቢ
ግመሎችና ሌሎች
እንስሳትን በመጠቀም
ለምርጫ ቀን የሚጠቅሙ
ቁሳቁሶች ተጓጉዘዋል፡፡