ምርጫውን በተሳካ
መልኩ ለማጠናቀቅ
አስፈላጊውን
ዝግጅት
ማድረጉን ቦርዱ
አስታወቀ
መጪው ግንቦት 7 የሚካሄደውን
የሕዝብ ተወካዮችና
የክልል ምክር ቤቶች
አባላት ምርጫ በተሳካ
ሁኔታ ለማጠናቀቅ
የሚያስፈልገውን
ዝግጅት በማጠናቀቅ
ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ
ብሔራዊ የምርጫ
ቦርድ አስታወቀ፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ
ከማል በድሪ ዛሬ
ለጋዜጠኞች እንደገለፁት
ለምርጫው የሚያስፈልጉ
ቁሳቁሶች በመላ
ሀጓሪቱ በሚገኙ
31,000 የምርጫ ጣቢያዎች
የተሰራጩ ሲሆን
ለምርጫ አስፈፃሚዎችም
አዳዲስ አሰራሮችን
ጨምሮ በድምፅ አሰጣጥ፣
ቆጠራና ውጤት አገላለፅ
ዙሪያ በሦስት ዙሮች
ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
በተለያዩ የፖለቲካ
ፓርቲዎች ለቦርዱ
የቀረቡ ቅሬታዎች
በየደረጃው በተቋቁሙ
የፓርቲዎች የጋራ
መድረክና ከቦርዱ
ጽሕፈት ቤት በሚላኩ
አጣሪ ቡድኖች ከተጣሩ
በኋላ ውጤቱ በሀገር
አቀፍ ደረጃ ለተቋቋመው
የጋራ መድረክ መቅረቡን
አስረድተዋል፡፡
የምርጫውን ነፃና ፍትሀዊነት
ይበልጥ ለማረጋገጥ
እስከአሁን ለ319
የውጭ ሀገር ታዛቢዎች
እውቅና መሰጠቱን
የጠቆሙት አቶ ከማል
ከተለያዩ ሀገራት
ኤምባሲዎች ለተወከሉ
ታዛቢዎች ፈቃድ
በመስጠት ላይ ነው
ብለዋል፡፡
የአገር ውስጥ ታዛቢዎችን
በተመለከተ እስካሁን
463 ለሚሆኑ ከኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን፣
ከኢትዮጵያ ወንጌላዊያን
ቤተክርስቲያንና
ከኢትዮጵያ እስልምና
ጉዳዮች ምክር ቤት
ለተውጣጡ ታዛቢዎች
ፍቃድ ተሰጥቷል፡፡ከእምነት ተቋማቱ
ታዛቢዎች ተጨማሪ
ቦርዱ በሚወስነው
መሠረት ለሌሎች
የሲቪክ ድርጅቶችም
ፈቃድ እንደሚሰጥ
አስታውቀዋል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች
የምረጡኝ ቅስቀሳ
ዘመቻ እስካሁን
በሰላማዊ መንገድ
እየተከናወነ መሆኑን
ጠቅሰው ፓርቲዎቹ
በሚቀራቸው የአንድ
ቀን የቅስቀሳ ጊዜ
ሰላማዊና ሕጋዊ
በሆነ መንገድ ቅስቀሳቸውን
ማካሄድ እንዳለባቸው
አሳስበዋል፡፡
ቦርዱ የፓርቲዎቹ
ቅስቀሳ ሰላማዊ
በሆነ መንገድ እንዲከናወን
ጥረት ሲያደርግ
መቆየቱን የገለፁት
ሰብሳቢው ባለፈው
ሳምንት መጨረሻ
ላይ የተካሄዱት
ሁለት ታላላቅ ስብሰባዎች
በሰላም መጠናቀቃቸው
የቅስቀሳ ሂደቱ
ሰላማዊ
በሆነ ሁኔታ የተካሄደ
ለመሆኑ አመላካች
ነው ብለዋል፡፡
ቦርዱ የመራጩን ግንዛቤ
ከፍ ለማድረግም
ከዚህ በፊት በራድዮና
በተለያዩ ድርጅቶች
አማካኝነት ሲያደርገው
የቆየው የሲቪክ
ትምሕርት እንደተጠበቀ
ሆኖ በቴሌቪዥንና
በተለያዩ ፖስተሮች
ስለድምፅ አሰጣጡ
ሂደት የተጠናከረ
ትምሕርት በመስጠት
ላይ ነው ብለዋል፡፡
የውጤት አገላለፅን
በተመለከተም አቶ
ከማል ሲያብራሩ
በምርጫ ጣቢያ ደረጃ
ጊዜያዊ ውጤት በምርጫው
ማግስት (ግንቦት
8)ለሕዝብ የሚገለፅ
ሲሆን እስከ ግንቦት
13 ባለው ጊዜ በምርጫ
ክልል ደረጃ ያለው
ውጤት ይፋ ይደረጋል፡፡
ሰኔ አንድ ቀን በአገር
አቀፍ ደረጃ የምርጫው
ውጤት ለሕዝብ እንደሚገለፅም
ሰብሳቢው አስረድተዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፕሬስ
ኦፊሰር ፡- ጌታሁን
አሞኝ 09643736
ረዳት ፕሬስ ኦፊሰር
፡
ሕይወት አለማየሁ
09487576