Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
   
 

ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም.

ብዛት ያላቸው መራጮች ድምፅ ሰጡ

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ምክር ቤት አባላት ምርጫ በመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ መራጮች ብዙዎቹ ወደምርጫ ጣቢያዎች ሄደው ድምፃቸውን እንደሰጡ የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት ሊቀመንበር አቶ ከማል በድሪ ገለፁ፡፡

በተጨማሪም የምርጫ ሂደቱ በሰላማዊና በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ እንዳለና፣ እስካሁን ክብደት ያለው ችግር ለቦርዱ ጽሕፈት ቤት እንዳልቀረበ ገልፀዋል፡፡

በመጀመሪያው ሰዓታት ላይ የምርጫ ሂደቱ የተጓተተ ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ ግን ሂደቱ እየተፋጠነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡  “የምርጫ አስፈፃሚዎች ተጨማሪ ሚስጢራዊ የድምፅ መስጫ ክፍሎችን በማዘጋጀት ሂደቱን አፍጥነውታል፡፡” ብለዋል፡፡

ማንኛውም ከ12፡00 ሰዓት በፊት በምርጫ ጣቢያ ግቢ ውስጥም ሆነ ውጪ የተሰለፈ መራጭ የመምረጥ መብት እንደሚኖረው አያይዘው ገልፀዋል፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ፕሬስ ኦፊሰር - ጌታሁን አሞኝ 09643736

ረዳት ፕሬስ ኦፊሰር ሕይወት አለማየሁ 09487576

 
     
     
       
           
           
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.