Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
 
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System

መጋቢት 8 ቀን 1997 ዓ.ም

ከ 26.2 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በመራጭነት ተመዘገበ

በመጪው ግንቦት 7 ቀን በሚካሄደው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለመሳተፍ ሕዝብ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

ማንኛውም የተመዘገበ መራጭ በድምፅ መስጫው ዕለት ስሙ፣ የትውልድ ቦታው፣ የምርጫ ጣቢያውን፣ የምዝገባ ቁጥሩንና ፊርማውን የያዘውን የመራጮች መታወቂያ ካርድ ይዞ መቅረብ እንደሚገባው ቦርዱ አሳስቧል፡፡

    የሶማሌ ክልልን ሳይጨምር በመላ ሀገሪቱ የተመዘገቡ መራጮች ስማቸው በመራጮች መዝገብ ላይ የሰፈረ ሲሆን የስም ዝርዝሩ በዚህ መዝገብ ላይ ያልሰፈረ ማንኛውም ሰው የመምረጥ መብት እንደማይኖረው ተገልጿል፡፡

    ከዚህ በላይ የተገለፀው ቁጥር የሶማሌ ክልልን የማይጨምር ሲሆን በሶማሌ ክልል በ23 ምርጫ ክልሎች የሚገኙ መራጮች ድምፅ የሚሰጡት በነሐሴ 15 ቀን 1997 ዓ.ም ይሆናል፡፡

     የሶማሌ ክልል የምርጫ ጊዜን ማስተላለፍ ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎች አርብቶ አደርና ከቦታ ቦታ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው ቦርዱ ባለው የሰው ኃይልና የቁሳቁስ አቅም ከሌላው የአገሪቱ ምርጫ ጋር በአንድ ጊዜ ማካሄድ ስለማይችል መሆኑ በዚሁ ጊዜ ተብራርቷል፡፡

 



Legal Framework    
Electoral Operations    
Maps & Data
Domestic & International Observers    
Election Results    
Photo Gallery    
   
 
   
   
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.