Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
   
 

ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም.

የድምፅ አሰጣጡ ሥርዓት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ለሦስተኛ ጊዜ የተደረገው የአገር አቀፍና ክልላዊ ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የምርጫውን ሂደት ሊያደናቅፍ የሚችል ችግር በ31,000ዎቹም የምርጫ ጣቢያዎች እንዳልተከሰተ አቶ ተስፋዬ መንገሻ የቦርዱ ጽሕፈት ቤት ምክትል ዋና ኃላፊ ገልፀዋል፡፡

“ብዙ መራጭ ባለበት የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫው ሂደት መጓተት፣ የድምፅ መስጫ ወረቀትና የመራጮች ማረጋገጫ ቀለም በበቂ ሁኔታ አለመኖርና በምርጫ ጣቢያዎች ለታዛቢዎች የሚሆን ቦታ መጥበብ ከአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የደረሱን አቤቱታዎች ናቸው” ብለዋል፡፡

የድምፅ መስጫ ወረቀትና የመራጮች ማረጋገጫ ቀለም በበቂ ሁኔታ ያልነበራቸው የምርጫ ጣቢያዎች በአንድ ምርጫ ክልል ከሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች እንዲወሰዱና የምርጫውን ሂደት እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡

እንዲሁም ተጨማሪ ሚስጢራዊ የድምፅ መስጫ ክፍሎችን በማዘጋጀት ብዙ መራጮች በአንድ ጊዜ እንዲመርጡ ተደርጓል፡፡ ይኼም የተደረገው ረጅም ሰልፍ ተሰልፈው ድምፅ ለመስጠት የሚጠባበቁ መራጮች ቶሎ ቶሎ እድል እንዲደርሳቸው ለማድረግ ነው፡፡

አቶ ተስፋዬ ጨምረው እንደገለፁት በሀገሪቱ በምስራቅና በደቡብ የሚገኙ የጅማና የአለማያ ዩኒቨርስቲዎች በምዝገባው ወቅት በነበሩ ችግሮች ምክንያት ለአንዳንድ የምርጫ ክልሎች  መራጮች የድምፅ መስጫ ወረቀቶች እንዳልደረሰ ገልፀዋል፡፡

ቦርዱ ጉዳዩን አጣርቶ በዚህ ምክንያት ሊመርጡ ያልቻሉትን ተማሪዎች በሚመጡት ሁለት ቀናቶች እንዲመርጡ ሁኔታውን ለማመቻቸት ወስኗል፡፡

የምርጫ ጣቢያዎቹ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት የሚዘጉ ቢሆንም ከዚሁ ሰዓት በፊት ማንኛውም በምርጫ ጣቢያው ውስጥም ሆነ ውጭ የተሰለፈ መራጭ የመምረጥ መብት ይኖረዋል፡፡ ይኼም በትዕግስት ተሰልፈው ያሉትን መራጮች የመምረጥ እድል እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ካለፉት ምርጫዎች ይልቅ በአሁኑ ምርጫ ብዛት ያላቸው መራጮች ድምፅ እንደሚሰጡ ይገምታል፡፡

ለበለጠ መረጃ ፕሬስ ኦፊሰር - ጌታሁን አሞኝ 09643736

ረዳት ፕሬስ ኦፊሰር ሕይወት አለማየሁ 09487576

 
     
     
       
           
           
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.