Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
   
 

ግንቦት 9 ቀን 1997 ዓ.ም

ቦርዱ በአለማያና በጅማ ዩኒቨርስቲዎች ለሚደረገው ምርጫ እየተዘጋጀ ይገኛል

ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. ድምፅ መስጫ ወረቀት ስላልደረሳቸው ድምፅ ያልሰጡ በጅማና በአለማያ ዩኒቨርቲዮች የሚገኙ ተማሪዎች ድምፃቸውን እንዲሰጡ በዩኒቨርቲዎቹ ለሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁሶች እየተላኩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

“ምርጫ ቁሳቁሶቹ ከዩኒቨርስቲዎቹ በተጠየቀው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ዝርዝር መሠረት እየተላከ ይገኛል::  ስለዚህም ድምፅ ያልሰጡ ተማሪዎች በሚመጡት ሁለት ቀናቶች ውስጥ ድምፃቸውን መስጠት ይችላሉ፡፡” ብለው አቶ ተስፋዬ መንገሻ የቦርዱ ጽሕፈት ቤት ዋና ኃላፊ ገልጸዋል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ በሀገሪቱ ከሚገኙ ከአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች ያገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ጥቂት ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በተለያየ ምክንያት ምርጫው እልተካሄደም በማለት አያይዘው ገልፀዋል፡፡

ስለምርጫው ውጤት በተመለከተ ጽሕፈት ቤቱ ከአዲስ አበባ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት የምርጫ ጣቢያዎች ውጤት እንደደረሰውና የክልሎች ውጤት ነገ ግንቦት 1ዐ ቀን 1997 ዓ.ም. ጀምሮ ለጽሕፈት ቤቱ እንደሚደርስ አስረድተዋል፡፡

ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ለጽሕፈት ቤቱ እንደደረሰ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቤቱታ እስከአሁን ተቀብሎ እንደሆነ ተጠይቀው በምርጫ ጣቢያዎችና በክልሎች አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎች አቤቱታዎችን ከተለያዩ ፓርቲዎች ተቀብለው ውሳኔ እያሳለፉ ይገኛሉ ብለው አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአቤቱታ አቀራረብ ሥርዓት መሠረት በድምፅ አሰጣጡ ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ለምርጫ ጣቢያው አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ችግሩ በተከሰተ በአምስት ሰዓታት ውስጥ መቅረብ አለባቸው፡፡  ቆጠራን በተመለከተ የሚቀርቡ አቤቱታዎች የምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ወደምርጫ ክልሉ/ወረዳ የምርጫ ጽሕፈት ቤት በደረሱ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለምርጫ ክልሉ/ወረዳ የምርጫ ጽሕፈት ቤት አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ መቅረብ አለባቸው፡፡

በአቤቱታ ሰሚ ኮሚቴው ውሳኔ ያልተስማማ አካል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ አቤቱታ ማቅረብ ይችላል፡፡  የቦርዱ ውሳኔ ተስማሚ ሆኖ ካልተገኘ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡

ለበለጠ መረጃ ፕሬስ ኦፊሰር - ጌታሁን አሞኝ 09643736
ረዳት ፕሬስ ኦፊሰር ሕይወት አለማየሁ 09487576

 
     
     
       
         
             
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.