ግንቦት
29 ቀን 1997 ዓ.ም.
ቦርዱ
በ 299 የምርጫ ክልሎች
ላይ የቀረቡ አቤቱታዎች
እየመረመረ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ
የምርጫ ቦርድ በግንቦት
7 ቀን 1997 ዓ.ም ምርጫ
ከተሳተፉ የፖለቲካ
ፓርቲዎች የቀረቡለትን
በ299 የምርጫ ክልሎች
ላይ የቀረቡ አቤቱታዎችን
በመርመር ላይ ነው፡፡
የቦርዱ የሕግ ባለሙያዎች
የቀረቡትን አቤቱታዎች
በዓይነት በዓይነታቸው
እየለዩ ሲሆን ቀጣዩ
ሥራ የቀረቡትን
አቤቱታዎች ከማሰረጃዎቹ
ጋር በማመሳከር
መጣራት የሚገባቸውን
መለየት ይሆናል፡፡
የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ
ከማል በድሪ እንዳሉት
ምርጫ ቦርድ አቤቱታዎችን
ለመለየት መስፈርቶችን
ያወጣል፡፡ መስፈርቶቹ
ለፖለቲካ ፓርቲዎች
ቀርበው ሃሳብ ከተሰጠባቸው
በኋላ ሥራ ላይ ይውላሉ
ብለዋል፡፡
ቅንጅት ለአንድነትና
ለዴሞክራሲ፣ ኢትዮጵያ
ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች
ሕብረት፣ ለኢትዮጵያ
ሕዝቦች አቢዮታዊ
ዴሞክራሲዊ ግንባርና
የኦርሞ ፌዴራሊስት
ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ
አብዛኞቹን አቤቱታዎች
ካረቀቡ ፓርቲዎች
መካከል ይገኙበታል፡፡
አቶ ከማል እንዳሉት
አቤቱታዎችን የሚያጣሩ
ከፓርቲዎች፣ አለምአቀፍ
ታዛቢዎችን ከምርጫ
ቦርድ የተውጣጡ
ኮሚቴዎች በዚህ
ሳምንት መጨረሻ
ተቋቁመው ሥራ ይጀምራሉ፡፡
የኮሚቴዎች ቁጥርና
የአባላት ብዛት
መጣራት በሚገባቸው
አቤቱታዎች ብዛት
መሠረት የሚወሰን
ይሆናል፡፡
ኮሚቴዎቹ ያጣሩበትን
ሪፖርት ለቦርዱ
የሚያቀርቡ ሲሆን
ቦርዱ ሪፖርቱን
ከመረመረ በኋላ
የመጨረሻ ውሳኔ
ይሰጣል፡፡ ቦርዱ
የጊዜያዊ ምርጫ
ውጤቱን ሊያፀና
ወይም ሊሰርዝና
አዲስ ምርጫ
እንዲካሄድ ሊወስን
ይችላል፡፡
ዳግም ምርጫ ሊካሄድ
የሚችለው በሕጉ
መሠረት ተፈፀመ
የተባለው ግድፈት
በምርጫ ውጤት ወሳኝነት
ካለው ብቻ እንደሚሆን
የቦርዱ ሰብሳቢ
ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ
የምርጫ ቦርድ የቀረቡለትን
አቤቱታዎች ለማጣራት
የሚወስደውን ጊዜና
በፓርቲዎች የቀረቡለትን
ጥያቄዎች መሠረት
በማድረግ ወጤት
በይፋ የሚገለፅበት
ቀን ከሰኔ 1 ወደ ሐምሌ 1 ቀን 1997 ዓ.ም ማስተላለፉ
ይታወቃል፡፡
ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ቁጥሮች ይደውሉ፡፡
የፕሬስ ኦፊሰር ጌታሁን አሞኘ 251 - 9 - 643738
ረዳት ፕሬስ ኦፊሰር ሕይወት አለማየሁ 251 - 9 - 487576 |