Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
   
 

ሰኔ 4 ቀን 1997 ..

ሶስት ዋና ዋና ፓርቲዎች ለብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የቀረቡት አቤቱታዎች በሚጣሩበት ሁኔታ ላይ የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ሕብረት፣ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ለብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ቅሬታ በሚሰማበትና በሚያጣራበት ሂደት ላይ የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በስምምነቱ መሠረት ሁሉም ፓርቲዎች በአገሪቱ የተካሄደው ምርጫ የሕዝቡን ፍላጐት ሙሉ በሙሉ በሚያረጋግጥና የህግ የበላይነትና የአገሪቱን ሕገመንግስታዊ ስርዓት ባከበረ ሰላማዊ መንገድ የተሳካ ፍፃሜ ላይ እንዲደርስ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የጋራ ሰነድ ፈራሚዎቹ ማንኛውንም የአመፅና ለአመፅ የማነሳሳት ተግባር ለማውገዝና ለአመፅ የማነሳሳት ተግባር ለማስቀረት ማድረግ ያላባቸውን ጥረት ሁሉ ለማድረግ ከማናቸውም የአመፅ ተግባራት ለመቆጠብና ለሁሉም ጉዳዮች ሕጋዊና ሰላማዊ መፍትሄ ለማሻት ተስማምተዋል፡፡

በምርጫ አፈፃፀም ላይ የታዩ ጉድለቶችን በማስመልከት የሚቀርቡ አቤቱታዎች በምርጫ ሕጉ መሠረት በተበጁ ሥርዓቶችና በፍርድ ቤቶች እልባት ማግኘት እንደሚኖርባቸውና እነዚህ አካላት የሚሰጧቸውን ውሣኔዎችም ለማክበር ተስማምተዋል፡፡

በግንቦት 22 ቀን 1997 .. በተካሄደው የፓርቲዎች የጋር መድረክ ላይ በተደረሰበት መግባባት መሠረት የጋራ ስምምነቱ ፈራሚዎች የምርጫ ቦርድ ቅሬታዎችን ለማጣራት ባቋቋማቸው አጣሪ አካላት በገንቢና ሚዛናዊ አግባብ ለመሳተፍ ዝግጁ ሆነዋል፡፡

የምርጫ ቦርዱ አቤቱታ መርማሪ አካል ምርመራውን አጠናቆ የመጨረሻ ውሣኔ ሃሳቡን ለቦርዱ ከማቅረቡ በፊት በቅሬታ መስማቱና በማጣራቱ ሂደቶች ላይ በመገኘት እስካሁን ባቀረቡት ማስረጃ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመስጠትም ሆነ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አዲስ መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ከማል በድሪ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ፓርቲዎቹ ይህንን ስምምነት መፈራረማቸው የአቤቱታ ማጣራቱን ሂደት ግልፅና የተቃና እንደሚያደርገው ያላቸውን እምነት ገልፀው ፓርቲዎቹ ለፈረሙት ሰነድ ተገዥ እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡

የስምምነቱን ሙሉ ጽሑፍ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ፡፡

ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ቁጥሮች ይደውሉ፡፡

የፕሬስ ኦፊሰር ጌታሁን አሞኘ   251 - 9 - 643738

ረዳት ፕሬስ ኦፊሰር ሕይወት አለማየሁ 251 - 9 - 487576

 
     
     
       
             
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.