Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
   
 

ሐምሌ 1 ቀን 1997 ..

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ 307 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የምርጫ ውጤት ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ 307 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የምርጫ ውጤት አረጋግጦ በዛሬው ዕለት ይፋ አደረገ፡፡

በቦርዱ ይፋ የተደረገው ውጤት ምንም አይነት አቤቱታ ያልቀረበባቸው እና አቤቱታ ቀርቦባቸው በቅሬታ ሰሚ አካሉ እና በቦርዱ በድጋሚ ውድቅ የተደረጉትን የምርጫ ክልሎች ያጠቃልላል፡፡  ቀሪዎቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የክልል ምክር ቤት አባላት የምርጫ ውጤት በቀጣይ ሳምንታት ይፋ ይደረጋል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ከማል በድሪ እንዳሉት 140 የምርጫ ክልሎች የማጣራት ሥራ እያከናወኑ ያሉት የአቤቱታ አጣሪ ኮሚቴዎች በሚቀጥለው ሳምንት ሥራቸውን አጠናቀው ይመለሳሉ፡፡  የቦርዱ አጣሪ ኮሚቴዎች በሚያቀርቡት የውሣኔ ሃሣብ መሠረት የመጨረሻ ውሳኔ እንደሚሰጥ የገለፁት አቶ ከማል ውሣኔው ጊዜያዊ ውጤቱን ማፅናት ወይም በምርጫ ክልሉ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በሙሉ ወይም በከፊል ዳግም ምርጫ ማካሄድ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

የቦርዱ የቅሬታ ሰሚ አካል 64 የምርጫ ክልሎች ላይ የአቤቱታ መስማት ሥራውን በሚቀጥለው ሳምንት ካጠናቀቀ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ታይቶ ምርመራ እንዲደረግባቸው የተወሰኑት የምርጫ ክልሎች ቀደም ሲል በቦርዱ እንዲመረመሩ ከተወሰኑት 14 የምርጫ ክልሎች ጋር በጋራ እንደሚጣሩ አቶ ከማል ገልፀዋል፡፡  ለሁለተኛ ጊዜ ታይተው ተቀባይነት ያላገኙ አቤቱታዎችም በይፋ የሚገለፁ ይሆናሉ፡፡  

23 የምርጫ ክልሎች ያሉት የሱማሌ ክልል ምርጫም በነሐሴ ወር የሚካሄድ ሲሆን ውጤቱም በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ይገለፃል፡፡  በዛሬው ዕለት ይፋ በተደረገው 307 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ውጤት ኢህአዴግ 139 መቀመጫዎችን በማግኘት እየመራ ሲሆን ቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ 93 የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሕብረት 42 መቀመጫዎችን በማግኘት ይከተላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ 524ቱን የምርጫ ክልሎች ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ለማድረግ ዕቅድ የነበረው ቢሆንም የቀረቡ አቤቱታዎች መብዛትና የማጣራት ሂደቱ ጊዜ መውሰድ አጠቃላይ ውጤቶቹን ለመግለጽ አላስቻለውም፡፡

 

 

ለበለጠ መረጃ በእነዚህ ቁጥሮች ይደውሉ፡፡

የፕሬስ ኦፊሰር ጌታሁን አሞኘ   251 - 9 - 643738

ረዳት ፕሬስ ኦፊሰር ሕይወት አለማየሁ 251 - 9 - 487576

 
     
     
       
             
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.