Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
መጋቢት 21 ቀን 1997 ዓ.ም


የኢትጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለተማሪዎች ሕብረት አመራር አባላት በካምፓሶች የሚደረገዉን የምርጫ ሂደት አስመልክቶ ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄደዉን ምርጫ ለሚያስፈፅሙ የተማሪዎች ካዉንስና ሕብረት አመራር አባላት ያዘጋጀዉ የሁለት ቀናት ሥልጠና ዛሬ ተጀመረ፡፡

ሥልጠናዉ የተማሪዎች ካዉንስል አመራር አባላት በየተቋሞቻቸዉ የሚያከናዉኑትን የተመራጮች ምዝገባና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት በተገነቢዉ ሁኔታ ለማስፈፀም የሚያስችላቸዉ ነዉ፡፡

የቦርዱ ምክትል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ መንገሻ ሥልጠናዉን ሲከፍቱ «ምርጫዉ ዲሞክራሲያዊና ነፃ እንዲሆን በሚደረገዉ ጥረት፤ ቦርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች ድምፅ እንዲሰጡ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ይገኛል» ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በአስር የመራጮች መዝገብ ላይ ከተመዘገቡ በኃላ በየተቋሞቻቸዉ እንዳሉ ከየመጡባቸዉ የምርጫ ክልሎች ለሚወዳደሩ ዕጩዎች ድምፃቸዉን ይሰጣሉ፡፡

በሥልጠናዉ በየደረጃዉ ስለሚገኙ ቋሚ የምርጫ አስፈፃሚዎች ምልመላ፣ ተግባርና ኃላፊነታቸዉ፣ የመራጮች ምዝገባና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት፣ በተጨማሪም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዉስጥ የምርጫ አፈፃፀም ሂደትን በሚመለከት ገለፃ ተደርጓል፡፡ በሥልጠናዉ ከዘጠኝ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተዉጣጡ የተማሪዎች ካዉንስል አመራር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም ምርጫ በየተቋሞቻቸዉ ሆነዉ እንዲሳተፉ ቦርዱ ሁኔታዎች እንዲያመቻች በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባቸዉ ይታወሳል፡፡

 
 
 
 
   
   
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.