መጋቢት 23
ቀን 1997
ብሔራዊ የምርጫ
ቦርድ መደበኛ ስብሰባውን
አካሄደ ውሣኔዎችም
አሳለፈ
የኢትዮጵያ
ብሔራዊ የምርጫ
ቦርድ በዛሬው ዕለት
(መጋቢት 23)ባደረገው
መደበኛ ስብሰባው
በተለያዩ ጉዳዮች
ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን
አሳለፈ፡፡
ቦርዱ ከተወያየባቸው
ጉዳዮች አንዱ በምርጫ
ሕጉ የምረጡኝ ዘመቻ
እንዳይካሄድባቸው
በተከለከሉ ቦታዎች
ቅስቀሳ ተካሂዷል
በሚል ከኢትዮጵያ
ሕዝቦች አብዮታዊ
ዴሞክራሲያዊ ግንባር
(ኢሕአዴግ) የቀረበው
ይገኝበታል፡፡
ቦርዱ
ይህንና ከዚህ በፊት
የደረሱትን ተመሳሳይ
ጥቆማዎች መሠረት
በማድረግ
ማንኛቸውም የእምነት
ተቋማት በግቢያቸው
ውስጥ የምረጡኝ
ቅስቀሳ እንዳይካሄድ
ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ
እንዳለባቸው አመልክቷል፡፡በግለሰቦችም
ሆነ በፖለቲካ ፓርቲዎች
በኩል የሚካሄዱ
ተመሳሳይ ህገወጥ
ድርጊቶች በሚያጋጥሙበት
ወቅት የኃይማኖት
ተቋማቱ ለቦርዱ
ማሳወቅ እንደሚገባቸው
አሳስቧል፡፡
በኢሕአዴግ
የቀረበውን በአዲስ
አበባ አስተዳደር
በአራዳ ክፍለ ከተማ
ወረዳ 14 እና 15 በገብርኤል
ቤተክርስቲያን
ተፈጽሟል ስለተባለው
ሕገወጥ የምረጡኝ
ቅስቀሳ በተመለከተ
ጉዳዩ በፖሊስ ተጣርቶ
አስፈላጊው ሕጋዊ
እርምጃ እንዲወሰድ
ወስኗል፡፡
ከዚህ
ሌላ ቦርዱ የመላው
ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ
ፓርቲ (መኢዴፓ) ለሕዝብ
ተወካዮች ምክር
ቤት እንዲወዳደሩ
የወከልኳቸውን
ሶስት ዕጩዎች ከዕጩነት
ሰርዣለሁ ሲል ለቦርዱ
የፃፈውን ደበዳቤ
ተመልክቷል፡፡
ቦርዱ
ጉዳዩን ከመረመረ
በኋላ በአሁኑ ጊዜ
የዕጩ ማቅረቢያ
ጊዜ ካለፈ ከአንድ
ወር በላይ የሆነውና
የድምፅ መስጫ ወረቀት
ታትሞ እየተዘጋጀ
ባለበት ወቅት ዕጩዎችን
ሰርዣለሁ በሚል
የቀረበው ማመልከቻ
ተቀባይነት የሌለው
ነው ሲል ወስኗል፡፡
ከአሁን
በኋላም የቦርዱ
ጽሕፈት ቤት ተመሳሳይ
ጥያቄዎችን የማያስተናግድ
መሆኑን ጨምሮ ገልጿል፡፡
ከዚሁ
ጋር በተያያዘ 13 የመኢዴፓ
አባላት አሁን ባለው
ጊዜያዊ የፓርቲው
አመራር አባላት
ምትክ ቋሚ አመራር
አባላትን እንድንመርጥ
ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራልን
ሲሉ ያቀረቡትን
ማመልከቻ ተመልክቷል፡፡
ቦርዱ
በሰጠው ውሣኔም
የዚህ አይነቱ ጥያቄ
በመተዳደሪያ ደንቡ
መሠረት ለፓርቲው
መቅረብ እንደሚኖርበት
ገልጾ የመኢዴፓ
አባላትም ጉዳዩን
በፓርቲያቸው በኩል
መፍትታት ካልቻሉ
በፍርድ ቤት መጠየቅ
እንደሚችሉ ገልጿል፡፡