Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 

መጋቢት 24 ቀን 1997 ዓ.ም.


የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር
መድረክ መሠረቱ፣ የሥነ ምግባር መመሪያ አፀደቁ

በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ሃገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ የሚካፈሉ 35 የፖለቲካ ፓርቲዎች በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የተዘጋጀውንና ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲወያዩበት የቆዩትን የጋራ የምክክር መድረክ መመስረቻ ሰነድንና የሥነ ምግባር መመሪያን ዛሬ (መጋቢት 24) በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በተከናወነ ሥነ ሥርዓት አፀደቁ፡፡

ከአገር አቀፍ ጀምሮ እስከ ምርጫ ጣቢያ ድረስ የሚመሰረተው የጋራ መድረክ ዋነኛ ዓላማ በምርጫ ሂደቱ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ አለመግባባቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመፍታት የምርጫውን ነፃነትና ርትአዊነት ማረጋገጥ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመሠረተውን መድረክ የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የሚመሩት ሲሆን በየክልሉ የሚገኙትን መድረኮች ደግሞ በየደረጃው የሚገኙ የምርጫ አስተባባሪዎች በበላይነት ይመሯቸዋል፡፡ የጋራ መድረኩ አባላት በሃገር አቀፍ ደረጃ በፀደቀው የሥነ ምግባር መመሪያ መገዛት ይኖርባቸዋል፡፡

አዲስ በፀደቀው የሥነ ምግባር መመሪያ መሠረት ማንኛውም ዕጩ ተወዳዳሪ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ የምርጫ ሕጉን፣ የምርጫ ቦርድ የሚያወጣቸውን ደንቦችና ሌሎች የአገሪቱ ሕግጋትን ሳይጥስ ኃሳብን በነፃ የመግለፅ፣ ደጋፊዎችን ለስብሰባ የመጥራት፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማዘጋጀትና እንዲሁም አግባብ ያላቸውን መረጃዎች እንዲሰጡት የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፡፡

በሥነ ምግባር መመሪያው መሠረት በወታደራዊ ካምፖች፣ ቤተክርስቲያናትና መስጊዶች፣ ትምሕርት በመካሄድ ላይ ባለባቸው ትምሕርት ቤቶችና መደበኛ የመንግሥት ሥራ በመከናወን ላይ ባሉባቸው ተቋማት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎችና አባላቶቻቸው የመንግሥት ቢሮዎችን፣ አውሮፕላኖችን፣ ተሽከርካሪዎችን፣ ተቀጣሪ ሠራተኞችንና ሌሎችንም የሕዝብ ንብረቶች ለምርጫ ቅስቅሳ ማዋል አይችሉም፡፡

በምርጫ ቅስቀሳ ጊዜ ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ዕጩ ተወዳዳሪ ሌሎች ዕጩዎችን ወይም የፖለቲካ ድርጅቶችን ማንቋሸሽ፣ መሳደብ ወይም ማዋረድ አይችልም፡፡ በዕጩዎች ወይም በወኪሎቻቸው ወይም በፖለቲካ ድርጅቶች የሚደረጉ የቅስቀሳ ንግግሮች፣ የሚወጡ መጽሔቶች፣ በራሪ ወረቀቶችና የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች የሌሎችን ዕጩዎች ወይም የፖለቲካ ድርጅቶች መብት የሚነኩ መሆን የለባቸውም፡፡

የብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ከማል በድሪ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የጋራ መድረኩ መመስረትና የሥነ ምግባር መመሪያው መጽደቅ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚደረገውን ጥረት የበለጠ ያግዛል፡፡ በምርጫ ወቅት በተወዳዳሪዎች መካከል ዴሞክራሲያዊ የመቻቸል ባሕልን ለማጎልበትም አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የጋራ መድረኩ መመስረትም ሆነ የሥነ ምግባር ደንቡ መጽደቅ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ዕጩዎች ሊከሰቱ የሚችሉትን ግንኙነቶችና አለመግባባቶች በመደበኛውና ሕጋዊ አሰራር እንዲፈቱ ከማድረግ ሊገድባቸው እንደማይች ተጠቁሟል፡፡

 

 
 
 
 
   
   
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.