Top Banner
Site Map Links Contact Us
Home
Election Day Countdown
About NEBE
What's New
Electoral System
Legal Framework
Electoral Operations
Maps & Data
Domestic & International Observers
Election Results
Photo Gallery
 
   
 

መጋቢት 27 ቀን 1997 ዓ.ም

ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የሃገር ውስጥ ታዛቢዋች የዕውቅና ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት መመሪያ አወጣ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በትናንትናው ዕለት (መጋቢት 27) ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሃገር ውስጥ ታዘቢዎችን የዕውቅና ፍቃድ አስጣጥ መመሪያ አፀደቀ፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የምርጫ የጊዜ ሠሌዳንም ይፋ አድርጓል፡፡

በመመሪያው መሠረት ታዛቢዎች ከየትኛውም ወገን ገለልተኛ መሆንና ቦርዱ ላወጣው የታዛቢዎች የሥነ ምግባር ደንብ ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡

ምርጫውን ለመታዘብ የሚያመለክት ማንኛውም ተቋም ድርጅቱ ሲመዘገብ ከዓላማዋቹ አንዱ ምርጫ መታዘብ መሆኑን የሚያሰረዳ ከመንግስት የተሰጠ ፊቃድ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

አመልካች ተቋማት ለታዛቢነት የሚያሰማሯቸው ግለሰቦች ማንነትና የመኖሪያ አድራሻ ለቦርዱ ጽ/ቤት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ቦርዱ የዕውቅና ፈቃድ ለተሰጠው ተቋምና በተቋሙ ለሚመደቡ ታዛቢዎች የመታወቂያ ካርድ ይሰጣል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚደረገውን ምርጫ በተመለከተ ከሚያዝያ 1-8 የመራጮች ምዝገባ ቀን እንዲሆን ወስኗል፡፡ ምዝገባው እንደተጠናቀቀም መጋቢት 9 ቀን የመራጮች መዝገብ በየተቋማቱ ግልፅ ሆኖ ይቆያል፡፡

ግንቦት 7 ቀን የድምፅ መስጫ ዕለት ሲሆን ከግንቦት 8 ቀን ጀምሮ የየተቋማቱ የድምፅ ቆጠራ በማዕከል በቦርዱ ጽ/ቤት የሚከናወን ይሆናል፡፡ በምርጫው የሚወዳዳሩ የፓለቲካ ፓርቲዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ የሚካሄደውን የመራጮች ምዝገባና የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ለመታዘብ በህጉ መሠረት አንድ አንድ ታዛቢዎቻቸውን መመደብ እንደማችሉ ቦርዱ አሰሰቧል፡፡

ከተለያዩ የፓለቲካ ፓርቲዎችና የግል ተወዳዳሪዎች የሚቀርቡትን ቅሬታዎችና አቤቱታዎች በተመለከተ የቦርዱ ጽ/ቤት ከፓለቲካ ፓርቲዎችየጋራ መድረክ አባላት ጋር በመሆን ችግሮች ተከስተዋል በተባሉባቸው አካባቢዎች በመሰማራት የማጣራት ሥራውን እንዲያከናውን ወስኗል፡፡

 
 
 
   
   
 
 
This site is designed by Afrolink Studio
Copyright © 2005 National Electoral Board of Ethiopia. All rights reserved.