|
|
|
|
|
|
|
|
 |
|
|
|
|
|
|
|
 |
|
| |
|
|
|
|
| |
ለፖለቲካ
ፓርቲዎች፣ ለጥምረቶች
እና
ለግል ተወዳዳሪዎች
ድጋፍ
የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
በግንቦት 7፣ 1997 ለሕዝብ
ተወካዮች ምክር
ቤት በሚደረገዉ
ምርጫ ለሚወዳደሩ
የፖለቲካ ፓርቲዎች፣
ጥምረቶችና የግል
ተወዳዳሪዎች ድጋፍ
ያደርጋል፡፡
ፖለቲካ
ፓርቲዎች፣ ጥምረቶች
የኢትዮጵያ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የምርጫ ቅስቀሳን
በተመለከተ ፖለቲካ
ፓርቲዎች ወይም
ጥምረቶች በዕቃና
በአገልግሎት የተመደበላቸውን
የብር መጠን የሚጠቀሙበት
ቀመር አዘጋጅቷል፡፡
ዕቃዎቹና አገልግሎቶቹ
የተገዙት በኢትዮጵያ
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
በፖለቲካ ፓርቲዎች
ወይም ጥምረቶች
ስም ነዉ፡፡ ቀመሩ
ለፖለቲካ ፓርቲዎች
ወይም ጥምረቶች
መጋቢት 9 ቀን፣ 1997
ዓ.ም. ቀን ተነግሯል፡፡
የብር
መጠን በተወዳዳሪ፤የፖለቲካ
ፓርቲ ወይም ጥምረት
በተወዳዳሪ 3460 ብር
ተመድቦለታል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲ
ወይም ጥምረት (75 ተወዳዳሪዎች
ካሉት) በጠቅላላዉ
259500 ብር ሊቀበሉ ይችላሉ፡፡
ከአንድ
በላይ ክልል ወስጥ
ለሚወዳደሩ የፖለቲካ
ፓርቲዎች ወይም
ጥምረቶች ተጨማሪ
ድጋፍ፤ እያንዳንዱ
ከአንድ በላይ ክልል
ዉስጥ የሚወዳደር
የፖለቲካ ፓርቲ
ወይም ጥምረት (በእያንዳንዱ
ክልል ውስጥ ከአንድ
በላይ ተወዳዳሪ
ያለው) በእያንዳንዱ
በሚወዳደርበት
ክልል የተመደበለትን
43250 ብር ይቀበላል፡፡
ሴት
ተወዳዳሪዎችን
ለሚያቀርብ የፖለቲካ
ፓርቲ ወይም ጥምረት
ተጨማሪ ድጋፍ፤
እያንዳንዱ ሴት
ተወዳዳሪ የሚያቀርብ
የፖለቲካ ፓርቲ
ወይም ጥምረት በእያንዳንዱ
የሴት ተወዳዳሪ
የተመደበለትን
2160 ብር ይቀበላል፡፡
ማንኛዉም
የተመደበለትን
ብር ያልተጠቀመ
የፖለቲካ ፓርቲ
ወይም ጥምረት ከጧቱ
3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ
7፡00 ሰዓት በ09 429932 መደወል
ይኖርበታል፡፡
የግል
ተወዳዳሪዎች
እያንዳንዱ
የግል ተወዳዳሪ
የተመደበለትን
3460 ብር የሚደርስ
የህትመት ስራ ከሶስት
ማተሚያ ቤቶች በብሔራዊ
የምርጫ ቦርድ በተወሰነው
በአንዱ ይከናወናል፡፡
የተመደበላቸውን
ገንዘብ ለመጠቀም
የሚፈልጉ የግል
ተወዳዳሪዎች ከሰኞ
እስከ አርብ ከጧቱ
3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ
7፡00 ሰዓት ድረስ በብሔራዊ
ምርጫ ቦርድ በሕንፃ
ሐ፣ ቢሮ ቁጥር 9
ተገኝተው መጠየቅ
አለባቸው፡፡
እስከ
ሚያዝያ 21፣ 1997 ከቀኑ
7፡00 ሰዓት ድረስ የተመደበለትን
ገንዘብ የማይጠቀም
ማንኛውም የፖለቲካ
ፓርቲ፣ ጥምረት
ወይም የግል ተወዳዳሪ
ዕድሉን ያጣል፡፡
ለፖለቲካ
ፓረቲዎች፣ ለጥምረቶች
እና ለሁሉም የግል
ተወዳዳሪዎች የተመደበው
የገንዘብ መጠን
እንደሚከተለው
ነው፤
|
|
|
|
ለግል እጩ ተወዳዳሪዎች
|
ጠቅላላ
የተመደበው የብር
መጠን (ብር) |
| 1,266,630 |
| የፖለቲካ ፓርቲው
/ የጥምር ፓርቲው
/ ስም |
ጠቅላላ
የተመደበው የብር
መጠን (ብር) |
| ቅንጅት ለአንድነት
እና
ዴሞክራሲ |
614,150 |
| የኢትዮጵያ ዴሞክራሲዊ
ኃይሎቸ
ሕብረት |
410,875 |
| የኢትዮጵያ ህዝቦች
አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ
ግንባር |
767,685 |
| የመላው ኢትዮጵያ
ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ |
192,460 |
| የአርጎባ ብሔረሰብ
ዴሞክራሲዊ ድርጅት
|
6,920 |
| የአርጎባ ሕዝቦች
ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ
|
3,460 |
| የአፋር ብሔራዊ
ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ |
29,840 |
| የአፋር አብዮታዊ
ዴሞክራሲያዊ
አንድነት ግንባር |
29,840 |
| የአፋር ነፃ አውጪ
ግንባር ፓርቲ |
6,920 |
| የኦሮሞ አቦ ነፃነት
ግንባር |
38,060 |
| የኦሮሞ ነፃነት አንድነት
ግንባር |
52,765 |
| የገዳ ስርዓት አራማጅ
ፓርቲ
|
151,375 |
| የኦሮሚያ ነፃነት
ብሔራዊ ፓርቲ |
121,100 |
| የኦሮሞ ፌደራሊስት
ዴሞክራቲክ
ንቅናቄ |
295,400 |
| ኢትዮጵያ ማህበረ-ዴሞክራሲ
ፌደራላዊ ፓርቲ |
3,460 |
| ትግሪ ወርጂ ብሔረሰብ
ዴሞክራሲያዊ አንድነት
ፓርቲ |
73,100 |
| የቤንሻንጉልና ጉሙዝ
ሕዝቦች
ዴሞክራሲዊ አንድነት |
24,220 |
| የሲዳማ አርነት ንቅናቄ |
67,900 |
| የሲዳማ ሀዲቾ ህዝብ
ዲሞክራሲያዊ ድርጅት |
67,900 |
| የሸኮና መዠንገር
ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ
ግንባር |
129,315 |
| የወላይታ ሕዝብ
ዴሞክራሲዊ ግንባር
|
32,000 |
| የኢትዮጵያ ፓን
አፍሪካኒስት ፓርቲ |
61,845 |
| የደንጣ
፣ ዱባሞ ክችንችላ
ዴሞክራሲዊ ድርጅት
|
6,920 |
| የደቡብ ኢትዮጵያ
ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች
አንድነት |
6,920 |
| የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ
ድርጅት |
3,460 |
| የጋምቤላ ሕዝቦች
ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ |
10,380 |
| የሶማሌ ሕዝቦች ዴሞክራሲዊ
ፓርቲ |
3,460 |
| የሐረሪ ብሔራዊ ሊግ
|
3,460 |
| የሐረሪ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ
ፓረቲ |
6,920 |
| የኢትዮጵያ ብሔራዊ
አንድነት ፓርቲ |
10,380 |
| የጋሞ ዴሞክራሲያዊ
ህብረት |
6,920 |
| የኢትዮጵያውያን
አንድነት
ዴሞክራሲያዊ ድርጅት |
3,460 |
| ድምር |
3,242,870 |
|
|
|
|
|
| |
|
|
|
|
| |
 |
|
|
|
| |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|